የንግድ ስራን በኢትዮጵያ መጀመር ወደሚለው ተግባራዊ ኮርስ እንኳን በደህና መጡ! በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ንግድ ለመጀመርም ሆነ ነባሩን ለማስፋት ይህ ኮርስ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን እና መመሪያዎችን ይሰጥዎታል እንዲሁም የኢትዮጵያን ገበያ ተግዳሮቶች እና እድሎች ለመዳሰስ ይረዳዎታል። የእርሶ ኢንስትራክተር እንደመሆኔ ከስኬቶች እና ውድቀቶች የተማርኩትን ጠቃሚ ትምህርቶችን ጨምሮ ከ10 አመት በላይ በንግዱ አለም ያካበትኩትን ልምድ ላካፍላችሁ ጓጉቻለሁ። በስራዬ ወቅት ከችርቻሮ ንግድ እስከ ሪል ስቴት ድረስ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን የመቃኘት እድል አግኝቻለሁ፣ አልፎ ተርፎም የተለያዩ ሀገራትን በመዞር በአለም አቀፍ የንግድ ልምዶች ላይ እውቀት ለመቅሰም ችያለሁ ። ይሁን እንጂ እንደ ኢንስትራክተር የሚለየኝ በኢትዮጵያ ልዩ የንግድ ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ልምድ ነው። በመጀመርያ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራ ለመጀመር እና ለመምራት ያሉትን ፈተናዎች እና ውስብስቦች መንገዶችን ላሳውቃችሁ መርጬያለሁ ፣ እና ይህን እውቀት የስራ ልምዴን ለእርስዎ ለማካፈል ፍቃደኛ ነኝ ። በዚህ ኮርስ፣ የህግ መስፈርቶችን፣ ባህላዊ ደንቦችን እና የገበያ ትሬንዶችን ጨምሮ ስለ ኢትዮጵያ የንግድ አካባቢ አጠቃላይ ግንዛቤ ያገኛሉ። እንዲሁም እንዴት የንግድ እቅድ ማዘጋጀት እንደሚችሉ፣ የገንዘብ ድጋፍን ማረጋገጥ እና ምርቶችዎን ወይም አገልግሎቶችዎን በብቃት ለገበያ ለማቅረብ ያሉ ተግባራዊ ክህሎቶችን ይማራሉ። በዚህ ኮርስ መጨረሻ፣ ንግድዎን በኢትዮጵያ ውስጥ በድፍረት ለመጀመር ወይም ለማስፋት የሚያስፈልጉት መሳሪያዎች እና ዕውቀት ይኖርዎታል። በዚህ የኢትዮጵያ የንግድ የዕድገት ጉዞ ላይ በመተጋገዝ አብረን እንስራ!