አዶቤ ፎቶሾፕ በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃይለኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉ የግራፊክ ዲዛይን ሶፍትዌር አንዱ እንደሆነ ያውቃሉ? የግራፊክ ዲዛይን ክህሎትዎን ወደ አዲስ ደረጃ ማሳደግ ከፈለጉ ይህ ኮርስ ለእርስዎ ተስማሚ ነው።
እንደ ልምድ የግራፊክ ዲዛይነር እና የፒስ አብ ክሬቲዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደመሆኔ መጠን ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ደንበኞች ጋር በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ የመሥራት እድል አግኝቻለሁ። ባለፉት አመታት፣ አዶቤ ፎቶሾፕን በመጠቀም ታዳሚዎን የሚማርኩ እና የሚስቡ ግራፊክስ ለመፍጠር ችያለሁ።
በዚህ ኮርስ ላይ አዶቤ ፎቶሾፕን በመጠቀም አስደናቂ የሆኑ ንድፎችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉትን አስፈላጊ መሳሪያዎችን እና ቴክኒኮችን አሳያችኋለሁ ። ከመሠረታዊ ነገሮች እንጀምራለን፣ ለምሳሌ ሶፍትዌሩን በደንብ ማወቅ ፣ የፋይል ቅርጸቶችን መረዳት እና በለየሮዎች እንዴት እንደምንሰራ እናያለን ። ከዚያ ከፍ ወዳሉ ቴክኒኮች እንሄዳለን፣ እንደ ፎቶ ማስተካከል፣ ቀለም መመጠን እና የፊደል አይነቶች (ታይፖግራፊ) እንማራለን።
በዚህ ኮርስ ስለ ቴክኒካዊ ችሎታዎች ብቻ አይደለም የምትማሩት ስለ ከቨር ዲዛይን ቲዮሪ፣ ስለአቀማመጥ (composition)፣ ሚዛን (balance) እና የቀለም ፅንሰ-ሀሳብ (color theory)፣ እነዚህም ሁሉ በአንድ ላይ ይህም ማራኪ እና ውጤታማ የሆኑ ንድፎችን ለመፍጠር ይረዳዎታል። በኮርሱ መጨረሻ ላይ፣ ለራሳችሁ ወይም ለድርጅቶች የሚሆን ንድፎችን ለመስራት አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት ይኖራችኋል ስለዚህ ምን ትጠብቃላችሁ? አሁኑኑ የግራፊክ ዲዛይን ችሎታዎችን ወደሚቀጥለው ደረጃ አሳድጉ!