እንግሊዝኛ ይማሩ፡ የመናገር እና የማዳመጥ ችሎታዎን ያሻሽሉ

  • ደረጃ : Intermediate
  • ቋንቋ : Amharic
  • ቆይታ : 13:00
  • ክፍሎች : 44
  • በሞባይል፣ በዴስክቶፕ እና በቲቪ ያገኛሉ
  • የኮሚኒቲው የህይወት ዘመን አባል ይሆናሉ
  • የማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ

ስለ ኮርሱ መግለጫ

በእንግሊዝኛ ለመግባባት ተቸግራዋል? ከሰዎች ጋር በአዲስ ቋንቋ መናገር ከባድ ሊሆን እንደሚችል እንረዳለን፣ ለዚህም ነው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከሰዎች ጋር በቀላሉ የመነጋገር ጥበብን እንድትማሩ ይህን የኦንላይን ኮርስ ያዘጋጀነው። የእኛ ኮርስ እንግሊዘኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋችው ላልሆኑ ሰዎች የቃላት ዕውቀታቸውን ለማስፋት እና በዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ከሰዎች ጋር በእንግሊዝኛ ቋንቋ መግባባት ለሚፈልጉ የተዘጋጅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም አዳዲስ ጓደኞች ለማፍራት፣ ከውጭ ሃገር ሰዎች ጋር የንግድ ስራ ለመስራት፣ የእንግሊዘኛ ፊልሞችን ያለማንም ዕርዳታ በራሳቸው ለመመልከት እንዲሁም ወደ ሌላ ሃገር ለማድረግ ለሚፍለጉ ሁሉ የተዘጋጀ ነው። እንግሊዘኛ አለምአቅፍ ቋንቋ እንደመሆኑ፣ የእንግሊዘኛ መሰረታዊ ዕውቀት በአብዛኛዎቹ አገሮች ውስጥ ለመስራት እጅግ አስፈላጊ ነው።ሆኖም፣ የእኛ ኮርስ የእንግሊዝኛ ችሎታዎን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል፣ ይህም አፍ መፍቻ ቋንቋችው እንግሊዘኛ እንደሆኑ ተወላጆች እንዲግባቡ እና በጣም የተወሳሰቡ ሃሳቦችዎን እንኳን በቀላሉ እንዲገልጹ ያስችልዎታል። ይህ ሁሉን አቀፍ ሥርዓተ-ትምህርት በእውነተኛ ህይወት ሁኔታዎች ላይ በማተኮር የሰዋስው፣ የቃላት አነጋገር እና የቃላት አጠራርን ጨምሮ ሁሉንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ መሰረታዊ ነገሮችን ይሸፍናል። ትምህርታችንን እንደጨረሱ በማንኛውም እንግሊዝኛ ተናጋሪ አገር በቀላሉ መጓዝ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ሌሎች ተጓዦች ጋር መግባባት፣ ንግድ ማካሄድ፣ ትምህርት መማር እና ሌሎችንም ማድረግ ይችላሉ፡፡ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ላልሆኑ ሰዎች የኛን ኮርስ ተደራሽ እና ቀላል ለማድረግ እንተጋለን፣ ስለዚህ ጀማሪም ሆኑ መካከለኛ ተናጋሪ፣ የእኛ ኮርስ ግቦዎትን ለማሳካት ይረዳዎታል።

መስፈርቶች

  • የኮምፒተር እና የኢንተርኔት መሰረታዊ ግንዛቤ
  • መሰረታዊ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ግንዛቤ (አስፈላጊ፣ ግን ግዴታ አይደለም)
  • የማይቆራረጥ የኢንተርኔት ግንኙነት እና የኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ
  • ይህ ኮርስ ለማን ነው?

  • የእንግሊዝኛ አነባበብ ቅልጥፍናን ማሻሻል የሚፈልጉ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ያልሆኑ ተናጋሪዎች
  • በእንግሊዘኛ የመግባባት ችሎታቸውን ማሻሻል ለሚፈልጉ ፍሪላንሰሮች እና የቢዝነስ ሰዎች
  • የመስማት ችሎታቸውን ማሻሻል የሚፈልጉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች
  • የእንግሊዝኛ የመግባቢያ ችሎታቸውን ማሻሻል ለሚፈልጉ
  • የእንግሊዘኛ አካዳሚክ ብቃት ፈተናን ማለፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች
  • እንግሊዝኛ በመናገር እና በማዳመጥ በራስ መተማመንን ማግኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው
  • የምትማሩት

    Testimonials

    • ደረጃ : Intermediate
    • ቋንቋ : Amharic
    • ቆይታ : 13:00
    • ክፍሎች : 44
    • በሞባይል፣ በዴስክቶፕ እና በቲቪ ያገኛሉ
    • የኮሚኒቲው የህይወት ዘመን አባል ይሆናሉ
    • የማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ