አስደናቂ ግራፊክሶችን ይስሩ፡ የአዶቤ ፎቶሾፕ ኮርስ 2024


  • ደረጃ : ጀማሪ
  • ቋንቋ : አማርኛ
  • ቆይታ : 8:00
  • የትምህርቶች ብዛት : 47
  • በሞባይል፣ በዴስክቶፕ እና በቴሌቪዥን ላይ መዳረሻ
  • የቴሌግራም ማህበረሰብ መዳረሻ
  • የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት

ስለ ኮርሱ

አዶቤ ፎቶሾፕ በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃይለኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉ የግራፊክ ዲዛይን ሶፍትዌር አንዱ እንደሆነ ያውቃሉ? የግራፊክ ዲዛይን ክህሎትዎን ወደ አዲስ ደረጃ ማሳደግ ከፈለጉ ይህ ኮርስ ለእርስዎ ተስማሚ ነው። እንደ ልምድ የግራፊክ ዲዛይነር እና የፒስ አብ ክሬቲዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደመሆኔ መጠን ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ደንበኞች ጋር በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ የመሥራት እድል አግኝቻለሁ። ባለፉት አመታት፣ አዶቤ ፎቶሾፕን በመጠቀም ታዳሚዎን ​​የሚማርኩ እና የሚስቡ ግራፊክስ ለመፍጠር ችያለሁ። በዚህ ኮርስ ላይ አዶቤ ፎቶሾፕን በመጠቀም አስደናቂ የሆኑ ንድፎችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉትን አስፈላጊ መሳሪያዎችን እና ቴክኒኮችን አሳያችኋለሁ ። ከመሠረታዊ ነገሮች እንጀምራለን፣ ለምሳሌ ሶፍትዌሩን በደንብ ማወቅ ፣ የፋይል ቅርጸቶችን መረዳት እና በለየሮዎች እንዴት እንደምንሰራ እናያለን ። ከዚያ ከፍ ወዳሉ ቴክኒኮች እንሄዳለን፣ እንደ ፎቶ ማስተካከል፣ ቀለም መመጠን እና የፊደል አይነቶች (ታይፖግራፊ) እንማራለን። በዚህ ኮርስ ስለ ቴክኒካዊ ችሎታዎች ብቻ አይደለም የምትማሩት ስለ ከቨር ዲዛይን ቲዮሪ፣ ስለአቀማመጥ (composition)፣ ሚዛን (balance) እና የቀለም ፅንሰ-ሀሳብ (color theory)፣ እነዚህም ሁሉ በአንድ ላይ ይህም ማራኪ እና ውጤታማ የሆኑ ንድፎችን ለመፍጠር ይረዳዎታል። በኮርሱ መጨረሻ ላይ፣ ለራሳችሁ ወይም ለድርጅቶች የሚሆን ንድፎችን ለመስራት አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት ይኖራችኋል ስለዚህ ምን ትጠብቃላችሁ? አሁኑኑ የግራፊክ ዲዛይን ችሎታዎችን ወደሚቀጥለው ደረጃ አሳድጉ!

መስፈርቶች

  • አዶቤ ፎቶሾፕ ሶፍትዌር የተጫነበት ኮምፒውተር
  • መሰረታዊ የኮምፒውተር ችሎታዎች

ይህ ኮርስ ለማን ነው?

  • ስለ ግራፊክ ዲዛይን መማር ለሚፈልጉ ጀማሪዎች
  • ለማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው እና ለማስታወቂያ ስራዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎችን መፍጠር ለሚፈልጉ የግብይት ባለሙያዎች
  • እንደ በራሪ ወረቀቶች፣ ብሮሹሮች እና ባነሮች ያሉ የራሳቸውን የገበያ ቁሳቁሶችን መፍጠር የሚፈልጉ አነስተኛ የንግድ ሥራ ባለቤቶች
  • ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የግራፊክ ዲዛይን ችሎታቸውን ማሻሻል የሚፈልጉ ተማሪዎች
  • አዶቤ ፎቶሾፕን በመጠቀም ፎቶግራፎቻቸውን ማሻሻል እና ማቀናበር ለሚፈልጉ ፎቶግራፍ አንሺዎች

ምን ይማራሉ

  • ትምህርት 1: የግራፊክ ዲዛይን መሰረታዊ ነገሮችን መረዳት
  • ትምህርት 2: የንድፍ መርሆዎች እና ኢለምንት
  • ትምህርት 3: የቀለም ንድፈ ሐሳብ
  • ትምህርት 4: ኮምፖዝሽን እና አቀማመጥ
  • ትምህርት 5: ታይፖግራፊ
  • ትምህርት 6: የአዶቤ ፎቶሾፕ መግቢያ
  • ፈተና

ይህንን ኮርስ አጋራ

ተገቢ ሰው ታውቃለህ? ሊንኩን አጋራ፤ ሲመለከቱ ወይም ሲመዘገቡ ሽልማት ታገኛለህ።

Powered by