ሙያሎጂ በተለያዩ መስኮች ላይ ኦላይን ኮርሶችን የሚያዘጋጅ ፣ የሚሸጥ እና የሚያስተዳድር አዲስ የመማሪያ መድረክ ነው። ቃሉ ሙያ እና ሎጂ ከሚሉ የሁለት ቃላት ጥምር የተመሰረተ ነው። ሙያ የአማርኛው ቃል ሙያ ሲሆን ሎጂ ማለት በግሪክ ጥናት ማለት ነው። ስለዚህ ሙያሎጂ የሙያ ጥናት ማለት ነው። እንዲሁም ማንኛውም ሰው አዲስ ክህሎት የሚማርበት እና ያለውን ችሎታ የሚያዳብርበት ቦታ ነው። አሁን ላይ በምንሰጣቸው የተለያዩ ኮርሶች ላይ ምዝገባ ጀምረናል።
ሙያሎጂ የተለያዩ ሙያ ነክ የሆኑ ክህሎቶችን እንደ ፎቶግራፍ ፣ ግራፊክስ ዲዛይን ፣ ፋሽን ዲዛይን ፣ ሙዚቃ ፕሮዳክሽን ፣ ስራ ፈጠራ ፣ ኢንቴሪየር ዲዛይን ፣ ጊታር ፣ ኬክ ፣ ጥፍርና አይላሽ እና ሊሎችንም እንሰጣለን።
ሀ. ብቁ ባለሙያዎች ( በሙያው ላይ በቂ ልምድ እና እውቀት ያካበቱ ናቸው)
ለ. ከፍተኛ ጥራት ያለው ( ምስል እና ድምጽ)
ሐ. በመረጡት ቋንቋ ኮርሶቹን ያገኛሉ።
መ. ለመማር ምቹ ነው ( በየትኛውም ቦታ ፣ በፈለጉት ሰዓት)
ሠ. ተግባራዊ ልምምድ እና ፈተና
ረ. ሁሉም ኮርሶች ፕሮጀክት አላቸው።
ሰ. ከባለሙያዎቹ እገዛ እና ክትትል በኮሚዩኒቲ
ሸ. በተመጣጣኝ ዋጋ
ቀ. በባለሙያው የተፈረምበት የማጣናቀቂያ ሰርተፍኬት ይሰጣል።
muyalogy.com ወይም ቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ በመግባት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ። ድህረ ገጻችን ለመመዝገብ በጣም ግልጽ እና ቀላል ነው።
የሙያሎጂ ኮርሶችን ለመማር እስማርት ስልክ ወይም ኮምፒውተር እና የኢንተርኔት አገልግሎት ያስፈልጋል።
የሞባይል ስልክ ፦ ለመመዝገብ
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዲጂታል የመክፈያ መንገዶችን ተጠቃሚ መሆን።
ለኮርሶቹ ያዘጋጀነው ዋጋ በጣም ተመጣጣኝ ሲሆን ክፍያችን በአንድ ኮርስ 2500 ብር ይሆናል። ነገር ግን አሁን የማስታወቂያ ቅናሽ ላይ ስለሆንን የኮርሱ ዋጋ 2000ብር ሆኗል።
አሁን ምዝገባ ላይ ስንሆን የመመዝገቢያ ዋጋውም 500 ብር ነው።
ክፍያ ለመፈፀም የቴሌብር ሱፐር አፕ ወይም ዌብሳይታችንን መጠቀም ይቻላል። እንዲሁም ሲቢኢ ብር ፣ አዋሽ ብር ፣ አሞሌ ፣ ፔፓል፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ እናት ባንክ ፣ ሄሎ ካሽ ፣ ኮፕ ኢብር ተጠቅመው ክፍያ መፈፀም ይችላሉ።
አዎ. የሙያሎጂ ኮርሶችን ኦላይን በ ዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት ወይም በሞባይል ማግኘት ይችላሉ።
ኮርሶቹ ከ3 እስከ 6 ሰአታት ባለው ጊዜ ውስጥ በተቀዳ የቪዲዮ ምስል ይቀርባሉ። እንዲሁም ኮርሶቹ በምዕራፍ እና በክፍል ይከፈላሉ።
አይ፣ የእኛ የደህንነት መመሪያ ኮርሶቹን ማጋራት፣ ስክሪን መቅዳት እና ማውረድ አይፈቅድም።
አሁን የምንሰጠው የኦላይን ኮርሶችን ብቻ ነው። ነገር ግን ከኦላይን ውጭ የሆነ የራሳችንን የሞባይል መተግበሪያ ለማዘጋጀት በሂደት ላይ ነን።
ሙያሎጂ የኮሚውኒቲ ፕላትፎርም ስላለው ኮርሶቹ ኦላይን ስለሆኑ ብቻቹን እየተማራቹ እንደሆነ ማሰብ የለባችሁም።
ከእርስዎ ጋር ተመሳሳይ ኮርስ የሚማሩ ተማሪዎች በብዛት ስለሚኖሩ ፕላትፎርማችን ከሌሎች ተማሪዎች እና ከአስተማሪዎቻችሁ ጋር የምትማማሩበትን መንገድ አዘጋጅቶላችኋል።
አድራሻችን ፦ ማምቡክ ህንጻ 7ኛ ፎቅ፣ መስቀል ፍላወር ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር፡ +251912637683
ኢሜል፡ hi@muyalogy.com
ሁሉንም ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን በመከተል የተለያዩ ዕለታዊ ይዘቶች ማግኘት ይችላሉ።
ሙያሎጂ ለባለሙያዎች ያስቀመጠው መስፈርቶች አሉት፣ ስለዚህ እነዚህን ማሟላት ከቻሉ ከሙያሎጂ ጋር አብሮ ለመስራት በራችን ክፍት ነው።
አዎ፣ ሙያሎጂ ኮርስዎን ሲያጠናቅቁ የምስክር ወረቀት ይሰጣል። የእኛ የምስክር ወረቀት ለጊዜው እውቅና ባይኖረዉም ወደፊት ኩባንያዎች ተመራጭ ስለሚያደርጉን ብቁ ባለሞያ እንድትሆኑ ይረዳችኋል።
አዎ፣ የሙያሎጂ ብቁ ተማሪዎች በሚኖራቸው ችሎታ ላይ የተለያዩ የሥራ ዕድሎች ይኖራቸዋል። ከእዚም ባለፈ የራሳቸው የንግድ ሥራ ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል።
በተጨማሪም ሙያሎጂ ከተለያዩ ስራ አገናኝ መድረኮች ጋር በጋራ ይሰራል።
የሙያሎጂ ኮርሶች መማር ፍላጎት ላለቸዉ ሁሉ የተዘጋጀ ነው። እንዲሁም ለተማሪዎች ፣ ለፍሪላንሰሮች ፣ ፍላጎታቸዉን መማር ለሚፈልጉ ፣ ሰራተኞቻቸውን ለማሳደግ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የተዘጋጀ ነዉ ።
ኮርሶቹ የሚዘጋጁት በአማርኛ ቋንቋ ቢሆንም በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለመቅዳት እና የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እቅድ ይዘናል። በተጨማሪም ኮርሶቻችን መስማት ለተሳናቸው ሰዎችም ተደራሽ እንዲሆን በጽሑፎች አዘጋጅተናል።
ለማስተማር ልዩ ፍላጎት ያላቸው እና በቂ ልምድ ያላቸው ብቁ አስተማሪዎች አሉን
የእኛ ኮርሶች የተማሪዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት እና የመማር ግባቸውን ለማሳካት እንዲረዷቸው የተዘጋጁ ናቸው
የእኛ ኮርሶች የዘመኑ ኢንዱስትሪ የሚከተላቸውን ምርጥ ልምዶች የሚያንፀባርቁ እና ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄዱ ናቸው
ተማሪዎቻችን በብቃት እንዲማሩ ለመርዳት የቪዲዮ ትምህርቶችን ፣ ተግባራዊ ልምምዶች ፣ ጥያቄዎችን ጨምሮ የተለያዩ የመማሪያ ዘዴዎችን እናቀርባለን
ለተማሪዎቻችን ቀጣይነት ያለዉ ድጋፍ እናደርጋለን በቀጥታ ክፍለ-ጊዜዎች፣ በኮሚኒቲ ግሩፖች እና በግል የተግባራዊ ክፍለ ጊዜዎችን እንሰጣለን
ትምህርቶቻችን የተማሪዎቻችንን ፍላጎታቸውን እያሟሉ መሆኑን ለማረጋገጥ ከተማሪዎቻችን ግብረ መልስ እንሰበስባለን
የሙያሎጂ ኢንስትራክተሮች በየዘርፉ የዓመታት ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ናቸው። እውቀታቸውን ለማካፈል እና ሌሎች እንዲማሩ ለመርዳት ፍላጎት አላቸው።
ሙያሎጂ ለእያንዳንዱ ኮርስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ወይም ግብዓቶችን በዝርዝር ያቀርባል።, እንዲሁም አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አስቀድመው የት እንደሚያገኙ ይጠቁማል.
ተማሪዎች አስፈላጊ መሳሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን በኪራይ እና በግዢ የሚያገኙበት የራሳችንን ዲጂታል መደብር ለመጀመር በመንገድ ላይ ነን።
ኮርሶቹ ስለሚጀምሩበት ቀን እና ሰዓት ተጨማሪ መረጃ እንደተጠናቀቀ እንልካለን።
በመጀመሪያ ወደ ረሱት የይለፍ ቃል ቁልፍ በመሄድ የይለፍ ቃልዎን እንደገና ያስጀምሩ። ይህ መንገድ የሚያስቸግሮት ከሆነ ወደ ዌብሳይቱ በመግባት የደንበኛ አገልግሎትን ማነጋገር ይችላሉ። የይለፍ ቃልዎን እንደገና ለማስጀመር ይረዳዎታል።
ሙያሎጂ ኦንላይን ኮርሶችን ያቀርባል። የኦንላይን ኮርስ በተከታታይ ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ በመደበኛነት የሚሰጡ የኦንላይን ላይ ትምህርቶች ሲሆኑ የእኛ የኦንላይን ኮርሶች ግን በእራስዎ ፍጥነት እንዲማሩ የተዘጋጁ ናቸው። ስለዚህ በራስዎ ፍጥነት እና በራስዎ ጊዜ መማር ይችላሉ።
አዎ፣ ከአንድ ኮርስ በላይ መውሰድ ይችላሉ። ነገር ግን፣የሚወስዱት የኮርሶች ብዛት በመማርያ ዘዴ፣ፕሮግራም እና በምትወስዶቸው ኮርሶች መስፈርቶች ይወሰናል።
አሁን ላይ ምዝገባ የሚካሄደዉ በስልክ ቁጥር ብቻ ነው። የተጠቃሚዎቻችንን ማንነት ለማረጋገጥ እና አስፈላጊ መረጃዎችን ለመላክ ስልክ ቁጥሮችን እንጠቀማለን። ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ከወዲሁ ይቅርታ እንጠይቃለን።
የሙያሎጂ ፕላትፎርም ኢንስትራክተሮችን ለማግኘት እንዲረዳዎ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማል ።
ኮምዩኒቲ ፦ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ውይይት ለማድረግ ያግዝዎታል። ኢንስትራክተሩ የእርስዎን ጥያቄ አይቶ ምላሽ መስጠት ይችላል።
ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ፦ በቀጥታ ሊያገኟቸው የሚችሉበት የቀጥታ ክፍለ ጊዜዎችን ያቀርባል ። የቀጥታ ክፍለ ግዜዎችም በተወሰኑ ጊዜያት የታቀዱ ናቸው፣ ስለዚህ መቼ ተገኝተዉ ኮርሱን እንደሚማሩ ለማየት የኮርሱን ፕሮግራም ማረጋገጥ ያስፈልግዎታል።